Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስትሮች በአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስትሮች፣ የፌደራል ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ በሚገኘው የችግኝ ተካለ መርሐ-ግብር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ፡፡

በዚሁ መሠረት የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላን (ዶ/ር)፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር እና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የየተቋማቸውን ሠራተኞች በመያዝ በችግኝ ተከላው ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው ዕለት ብቻ 600 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች አረጓዴ ዐሻራቸውን እያኖሩ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.