በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞች የመትከል መርሐግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ንጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎችና የአከባቢው ነዋሪዎች አረንጓዴ አሻራቸውን እያኖሩ ነው፡፡