Fana: At a Speed of Life!

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዩቲዩብ ተከታይ ቁጥር ክብረወሰን ሰበረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ90 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ በዩቲዩብ ብዙ ተከታይ በማግኘት ክብረወሰን አሻሽሏል፡፡

የ39 ዓመቱ የአል ናስር አጥቂ ዩአር  ክርስቲያኖ የተሰኘ ዩቲዩብ ገጹን በኤክስ ገጹ ባስተዋወቀ 90 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 1ሚሊየን በላይ ተከታይ ማፍራት ችሏል፡፡

በዚህም 90 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ በዩቲዩብ ብዙ ተከታይ በማግኘት ክብረወሰን መስበሩ ነው የተገለጸው፡፡

ክርስቲያኖ የዩቲዩብ ገጹን ይፋ ካደረገ አንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥም 20 ሚሊየን የሚደርሱ ተከታዮች ማፍራት መቻሉ ተገልጿል፡፡

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዩቲዩብ ገጹ በተጨማሪ በኤክስ 112 ነጥብ 5 ሚሊየን፣ በፌስቡክ 170 ሚሊየን እንዲሁም በኢንስታግራም 636 ሚሊየን ተከታዮች አሉት፡፡

ሮናልዶ ከዩቲዩብ ገጹ በተጨማሪ በትዊተር 112 ነጥብ 5 ሚሊየን፣ በፌስቡክ 170 ሚሊየን እንዲሁም በኢንስታግራም 636 ሚሊየን ተከታዮች አሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.