የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ እየተወያዩ ነው፡፡
በውይይቱ የክልሉ ም/ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ የሰሜን ምሥራቅ እዝ ዋና አዛዣ ጄኔራል አሰፋ ቸኮልና በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ተገኝተዋል።
እንዲሁም የደቡብ ወሎ ዞን፣ የሰሜን ወሎ ዞን፣ የደሴ፣ የኮምቦልቻ እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
የሥራ ሃላፊዎቹ አሁን ላይ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ እየመከሩ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡