Fana: At a Speed of Life!

አቶ አረጋ ከበደ የክልሉ ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ዓሻራውን የማኖር ተግባር አካል እንዲሆን  የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር  አረጋ ከበደ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

ርእሰ መሥተዳድሩ በነገው ዕለት ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

 

አቶ አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው”የአረንጓዴ ዓሻራ መርሐ ግብር የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ ትውልድ ተሻጋሪ እና ምንዳ አመንጭ ተግባር ነው “ብለዋል፡፡

 

በመሆኑም በዚህ ታላቅ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ህዝብ ባለበት አካባቢ የትውልድ ዓሻራውን የማኖር ተግባር አካል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.