አቶ አወል የክልሉ ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ህዝብ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በንቃት እንዲሳተፍ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በክልሉ ለሚከናወነው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም የክልሉ ህዝብ ነገ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተካሄዱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን እንደገለጹም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡