አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከብሪታንያ የልማት፣ የሴቶች እና የእኩልነት ሚኒስትር ዴዔታ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከብሪታንያ የልማት፣ የሴቶች እና የእኩልነት ሚኒስትር ዴዔታ አኔሊሴ ዶድስ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ብሪታንያ ለኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋር መሆኗን አምባሳደር ታዬ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም በተለያዩ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡