ብልጽግና ፓርቲ ለጎፋ ዞን ተጎጂዎች የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በጋራ ለጎፋ ዞን ተጎጂዎች የሚሆን የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግናፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ለክልሉ መንግስት አስረክቧል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት÷አደጋው አሳዛኝና ከሌሎች አደጋ ሁሉ የተለየ የሰው ልጅ ለሰው የሚከፍለውን የመስዋዕትነት ጥግ ያሳየ ነው ብለዋል።
የአደጋው አስከፊነት ከኢትዮጵያ አልፎ አለምን ያስደነገጠ መሆኑን በመግለጽ የኢትዮጵያ ሕዝብም የመረዳዳት ባህሉን አጉልቶ ያሳየበት ነው ብለዋል፡፡