ሁሉን አቀፍ የባንክ አሰራርን ተደራሽ ማድረግ ኢንቨስትመንትን እንደሚያበረታታ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው ዓለም አቀፍ ወለድ አልባ የባንክ አሰራርና ታካፉል ዋስትና ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሀመድ በዚህ ወቅት÷ከወለድ ነፃ የሆነ የባንክ አገልግሎት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፍላጎት ከማርካት በተጨማሪ የአምራች ኢንዱስትሪውን ኢንቨስትመንት እንደሚያበረታታ ገልጸዋል፡፡
ከወለድ ነፃ የሆነ የባንከ ስርዓት መዘርጋት መንግስት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተገበረ ካላቸው ተግባራት አንዱ መገለጫ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
ስለሆነም መንግስት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከዓለም አቀፍ ኢስላማዊ የባንክና ኢኮኖሚ ማዕከል አልሁዳ ጋር በትብብር መስራቱን ይቀጥላል ማለታቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡