Fana: At a Speed of Life!

የፖክሮቭስክ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ዩክሬን አዘዘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ አጸፋዊ እርምጃ በመውሰድ ወደ ፖክሮቭስክ መገስገሷን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ ዩክሬን ማዘዟ ተሰምቷል፡፡

ዩክሬን ከሳምንታት በፊት ወደሩሲያ ግዛት ዘልቃ መግባቷ የሚታወስ ሲሆን ፥ ይህንንም የሁለቱ ሀገራት መንግስታት ማመናቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ሩሲያ አጸፋዊ ምላሽ እየሰጠች ባለችበት የፖክሮቭስክ ከተማ የሚኖሩ ሕጻናት ያሏቸው ቤተሰቦች ቀያቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቋ ተመላክቷል፡፡

የአካባቢው ባለስልጣናት እንደተናገሩት ፥ አሁን ላይ የሩሲያ ጦር ወደ ከተማዋ በፍጥነት እየገሰገሰ ነው፡፡

በዚህም ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ከተማዋን እና ሌሎች በአቅራቢያ ያሉ ከተሞችን እና መንደሮችን ለቀው መውጣት አለባቸው ነው ያሉት ።

ፖክሮቭስክ የዩክሬን ዋና የመከላከያ ምሽግ እና በዶኔትስክ ቀጣና ቁልፍ የሎጂስቲክስ ማዕከል አንዷ መሆኗን ጠቅሶ የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.