Fana: At a Speed of Life!

የቡሄ በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከበረ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ታቦር (የቡሄ) በዓል በደብረ ታቦር ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል፡፡

በዓሉ በኢትዮጵያ ክረምቱ አልፎ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት፣ ችቦ የሚበራበት እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ-መለኮቱን የገለጠበት እና ድምጸ-መለኮት የተሰማበት ጊዜ በመሆኑ የብርሃን (የቡሄ) በዓል በመባል ይታወቃል፡፡

የቡሄ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ነሐሴ 13 የሚከበር ሲሆን÷ በደብረ ታቦር ከተማም በርዕሰ-አድባራት ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሐይማኖታዊ ሥርዓቱ በሚያዘው መሰረት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

በተጨማሪም በፓናል ውይይትና በሌሎች ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን÷ በዚሁ ወቅትም በዓሉን ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በባለቤትነት ይዞ እንዲያስቀጥለው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.