Fana: At a Speed of Life!

ለላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነት መትጋት ይገባል- አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የበጀት ዓመት ለላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነት በትጋት መሥራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው አስገነዘቡ፡፡

የክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ አቶ እንዳሻው በሰጡት የሥራ መመሪያ÷ በክልሉ የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ለላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነት መሥራት ይገባል ብለዋል።

አመራሩ የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ሥራውን በውጤታማነት ማሳካት እንደሚጠበቅበት እና ከ2017 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት ፊርማ በኋላ ፈጥኖ ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በተቋማት የሚስተዋለውን ብልሹ አሠራር መታገል እንደሚገባ አሳስበው÷ ሌብነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና ሌሎች መሰል የአሠራር ማነቆዎችን መፍታት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡

በሁሉም ዘርፍ ተገቢውን የድጋፍ እና ክትትል ስራ ማጠናከር እንዲሁም በተቋማት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ላይ ማተኮር እንደሚገባም ነው ያብራሩት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.