Fana: At a Speed of Life!

አርብቶ አደሩ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ፕሮግራም ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሩ የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ፕሮግራም ይፋ ሆነ።

የግብርና ሚኒስቴር ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ጋር የፕሮግራም ስምምነቱን ተፈራርሟል፡፡

የስምምነት ፊርማውን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የፋኦ ተወካይ ፋራዪ ዚሙድዚ ፈርመዋል።

መርሃ ግብሩ በአራት ድንበር ዘለል የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚተገበር ሲሆን ሰባት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን ይሸፍናል ተብሏል፡፡

ፕሮግራሙ ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የ47 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ የሚተገበር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6 ነጥብ 25 ሚሊየን ዩሮ በኢትዮጵያ የአርብቶ አደር አካባቢዎች የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ እንደሚውል ተመላክቷል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ የሚገኙ አርብቶ አደር የማህበረሰብ ክፍሎች የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የመቋቋም አቅማቸውን ያሳድጋል መባሉን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.