Fana: At a Speed of Life!

የህዝብን መሰረታዊ የሠላምና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እሰራለሁ – ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የህዝቡን መሰረታዊ የሠላምና የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።

የክልሉ ምክር ቤት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ዛሬ መሾሙ ይታወቃል፡፡

አዲሷ ተሿሚ በዚህ ወቅት÷ የክልሉን ህዝብ ለማገልገል የተሰጣቸውን ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት በመወጣት ክልሉን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሻገር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና ልማትን ለማስቀጠል የተጀመሩ ሥራዎች በሁሉም መስክ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተናግረው የክልሉ ሕዝብም ለተጀመረው ለውጥ አስተዋጽኦውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

እንዲሁም የህዝቡን የሰላምና የልማት ጥያቄ ለመመለስ ሁሉም አካላት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው መናገራቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.