የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ነገ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ጊዜ 3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ነገ እንደሚካሄድ የክልሉ ምክር ቤት አስታውቋል።
ምክር ቤቱ ነገ በጋምቤላ ከተማ 6ኛ የምርጫ ጊዜ 3ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ለአንድ ቀን በሚካሄደው ጉባኤ ምክር ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል።