Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለአትሌቶች ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በፓሪሱ ኦሊምፒክ በማራቶን ውድድር ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኘው አትሌት ታምራት ቶላ የኮማንደርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

ኮሚሽኑ በተመሳሳይ ለሌሎች አትሌቶችም ማዕረግ ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ለአትሌት ትግስት አሰፋ የምክትል ኮማንደርነት፣ ለአትሌት ለሜቻ ግርማ የዋና ኢንስፔክተር፣ ለአትሌት ሲሳይ ለማ የዋና ኢንስፔክተር እንዲሁም ለአትሌት መገርቱ ዓለሙ የረዳት ኢንስፔክተርነት ማእረግ መስጠቱ ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.