Fana: At a Speed of Life!

በ1500 ሜትር ማጣሪያ ጉዳፍ ፀጋይና ድርቤ ወልተጂ ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1500 ሜትር የሴቶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ አልፈዋል፡፡

በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የዛሬ መርሐ-ግብር የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ምሽት ላይ ተካሂዷል፡፡

አትሌት ድርቤ ወልተጂ 1ኛ ደረጃ እንዲሁም አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 4ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

በአንጻሩ የ1 ሺህ 500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ብርቄ ኃየሎም ለፍፃሜ ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.