ባንኩ ዛሬ በልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ሸጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡
ባንኩ ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደውን የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።
በዚህም ዛሬ በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድን የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡
በጨረታው 27 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን÷ የዛሬው አማካይ ዋጋም የነገ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ መገለጹን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ÷ ተግባራዊ የተደረገው የባንክ ምንዛሪ ዋጋ ከትይዩ የገበያ ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት መቀራረቡን የሚያሳይ ተጨባጭ ውጤት መገኘቱ አስደሳች መሆኑን ገልጸዋል፡፡