Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያና ኢራን በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት ኢራን ቴህራን የገቡት የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሃፊ ሰርጌይ ሾይጉ በተለያዩ የሁለትዮሽ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ከቴህራን ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ሾይጉ የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ ከፍተኛ አዛዥ እና የኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፀሃፊ ከሆኑት ሪር አድሚራል አሊ አክባር አሕመድ ጋር ተገናኝተው መክረዋል ነው የተባለው።

በተጨማሪም ሾይጉ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እና የኢራን ወታደራዊ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም መሀመድ ባገሪ ጋርም ተገናኝተው መክረዋል ተብሏል።

በዚህም “ሩሲያ በአስቸጋሪ ጊዜያት ከኢራን ህዝብ ጎን ከቆሙት ሀገራት መካከል አንዷ ናት” ሲሉ ፔዜሽኪያን ማመስገናቸውን ጠቅሶ የዘገበው ሬውተርስ ነው፡፡

አክለውም፥ በኢራን እና በሩሲያ መካከል ያለው የጋራ አቋም ብዝሃ-ሃይልን በማስተዋወቅ ወደ የላቀ ዓለም አቀፍ ደህንነት እና ሰላም ያመራል ብለዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ በበኩሉ ባወጣው ዘገባ፤ የሰርጌይ ሾይጉ ጉብኝት ኢራንና እስራኤል ውጥረት ውስጥ በገቡበት ወቅት መሆኑን አንስቶ፤ አሜሪካና አጋሮቿ በቀጣናው እየተካረረ የመጣውን ቀጣናዊ ቀውስ መፍትሄ ለማበጀት እየመከሩ እንደሆነ ጠቅሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.