ቲክቶክ የኦንላይን ሱስ ስጋትን ለመከላከል ሲባል የሽልማት ገጽታዎችን ለማንሳት ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቲክቶክ በተለይም ልጆች በስክሪን ላይ እንዲቆዩ ለማበረታታት ጥቅም ላይ ያዋላቸውን የሽልማት ገጽታዎች ለማንሳት መስማማቱን የአውሮፓ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ኮሚሽን አስታውቋል።
በፈረንጆቹ የካቲት ወር ላይ ሥራ ላይ የዋለው እና ትላልቅ ዲጂታል መድረኮችን በመቆጣጠር ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተጠያቂነት ያለው የኦንላይን ምህዳርን ለማረጋገጥ በ27 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የዲጂታል አገልግሎቶች ሕግ መሰረት የተወሰነ የመጀመሪያ የምርመራ መፍትሄ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ገጹን በሕጋዊ መንገድ ለማረቅ የተደረሰው ውሳኔ ለመላው የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ኢንዱስትሪዎች ግልጽ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ሲሉ የአውሮፓ የዲጂታል ጉዳዮች ኮሚሽነር ማርግሬቴ ቬስታገር መናገራቸውን አይሪሽ ኤግዛማይነር ዘግቧል።