Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጉጂ ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በጉጂ ዞን የተለያዩየልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በዞኑ አዶላ ሬዴ ወረዳ ጉናጮ ቀበሌ በክላስተር እየለማያለን በቆሎ ተመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም በወረዳው አንፋራራ ቀበሌ በ25 ሺህ 650 ሔክታር ላይ በክላስተር እየለማ የሚገኝን ቡና ጎብኝተዋል፡፡

እንዲሁም በዞኑ ቦሬ ወረዳ የተቀናጀ የእንስሳት ሃብት ልማትን ተመልክተዋል፡፡

በተመሳሳይ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የተለያዩ ሚኒስትሮች በምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ ከላል ቀበሌ በክላስተር እየለማ ያለ ቡና ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ አቶ ሽመልስን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.