Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ዜጎቻቸው በአስቸኳይ ከሊባኖስ እንዲወጡ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካን ጨምሮ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ ፣ ስዊድን፣ ካናዳ እና ጆርዳን ዜጎቻቸው በአስቸኳይ ከሊባኖስ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ማሳሰቢያው የተላለፈው የሃማስ የፖለቲካ ኃላፊ እስማኤል ሃኒያህን ግድያ ተከትሎ ኢራን አፀፋ እንደምትስጥ መዛቷን ተከትሎ ነው፡፡

አሜሪካ በሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎቿ ማንኛውንም የበረራ ትኬት ተጠቅመው በአስቸኳይ ከሀገሪቱ እንዲወጡ አሳስባለች፡፡

ዛሬ ማለዳ ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል በምትገኘው ቢየት ሂለል ከተማ በርካታ ሮኬቶችን ማስንጨፉ እና በመካከላቸው የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ በሊባኖስ በርካታ በረራዎች መሰረዛቸው ተሰምቷል፡፡

አሜሪካ የእስራልን ጦር ለመርዳት በሚል የጦር መርከቦቿን እና ተዋጊ ጄቶችን ወደ ስፍራው ማሰማራቷን የገለፀች ሲሆን÷ ብሪታንያም ወታደራዊ መርከቦቿን እና የአየር ኃይሏን በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ማዘዟን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.