Fana: At a Speed of Life!

ኮሌጁ የካንሰር በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የቅንጅት ሥራዎችን ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የካንሰር በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከአጋር አካላት ጋር በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከአፍሪካ የምርምርና ሥልጠና ማዕከል፤ በአፍሪካ በካንሰር በሽታ ዙሪያ ጥናትና ምርምር ከሚያደርጉ ተቋማት ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡

የምክክሩ ዓላማ በአፍሪካ ደረጃ ያለውን የካንሰር ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችና ስጋቶች ምንነትና በጋራ በመሥራት ለውጥ ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የካንሰርና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ምርምር ክፍል አስተባባሪ አዳሙ አዲሴ (ዶ/ር)÷ ካንሰር በአፍሪካ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አንስተዋል፡፡

የዛሬው ውይይትም የበሽታውን አሳሳቢነት ለመቀነስ ችግር ፈቺ ምርምሮች ላይ ማተኮርን በሚመለከትና በዘርፉ ያሉ ተዋንያን ምን መሥራት እንደሚገባቸው በሚሉ ሀሳቦች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ ለማበጀት የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በአፍሪካ የካንሰር በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ መሪዎች ትኩረት መስጠት ይገባቸዋል ሲሉም ዶክተር አዳሙ ተናግረዋል።

በተለይም ሴቶች ስለጡትና ስለ ማህጸን በር ካንሰር ግንዛቤ እንዲኖራቸው በየጊዜው ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲበረታቱ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በአፍሪካ የካንሰር በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ከአጋር አካላት ጋር በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን መጠቆማቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.