አሜሪካ የጦር ጄቶችንና የጦር መርከቦችን ለእስራዔል ልትልክ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን በእስራኤል ላይ መዛቷን ተከትሎ አሜሪካ የጦር ጄቶችንና የጦር መርከቦችን ለእስራዔል ልትልክ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
አሜሪካ ተጨማሪ የጦር መርከቦችን እና ተዋጊ ጄቶችን ወደ መካከለኛዋ ምስራቅ ሀገር እስራዔል እንደምትልክ ፔንታጎን የገለጸ ሲሆን ፥ ይህም እስራኤልን ከኢራንና አጋሮቿ ጥቃት እንድትከላከል ለማገዝ እንደሆነ ነው የገለጸው፡፡
የሚሳኤል መከላከያ ሃይል ለማሰማራት ከፍተኛ ዝግጁነት ላይ መሆኑም ነው የተጠቆመው፡፡
በተጨማሪም አሜሪካ ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ እሰጣለሁ ስትልም ከእስራዔል ጎን መቆሟን አስታውቃለች እንደፔንታጎን መግለጫ፡፡
በኢራን የሐማስ መሪ ኢስማኢል ሃኒዬ እና የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦላ ቁልፍ አዛዥ መገደላቸውን ተከትሎ በቀጣናው ውጥረት መንገሱ ተሰምቷል፡፡
የኢራን መሪ አያቶላ ክሃሜኒ በበኩላቸው ፥ እስራዔል በሃኒዬ ግድያ ምክንያት ከባድ ቅጣት ይጠብቃታል ማለታቸውን አስታውሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡