Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት ምክንያት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚውል 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ መሀዲ(ዶ/ር) ፥ ምክር ቤቱ አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ ሃዘኑን ሲገልጽ እንደቆየ ገልጸዋል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንዲውልም 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ነው ያስታወቁት።

በምክር ቤቱ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ስለሺ ኮሬ(ዶ/ር ኢ/ር) በበኩላቸው ፥ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ምክር ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጅነር ዳግማዊ አየለ ለተደረገው ድጋፍ በተጎጂዎቹ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.