Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በጎፋ ዞን አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ14 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ14 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሰብዓዊ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያስረከቡት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) በአደጋው የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው፤ ለተጎዱ ወገኖች መፃናናትን ተመኝተዋል።

ኮምሽኑ ለተጎጂዎች 12 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እና 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት ሰብዓዊ የቁሳቁስ ድጋፍ በዓይነት÷ በአጠቃላይ የ14 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም አበርክቷል፡፡

ኮሚሽኑ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች መልሶ ለማቋቋም የሚያደርገውን ጥረት በቀጣይም የሚደግፍ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረቡን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.