Fana: At a Speed of Life!

በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድር ኢትዮጵያ 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው ኦሊምፒክ በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ወንዶች ውድድር ምስጋናው ዋቁማ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ።

በውድድሩ ኢኳዶር ስታሸንፍ፣ የብራዚልና የስፔን አትሌቶች ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል።

አትሌት ምስጋናው ዋቁማ 1 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን በስድስተኛነት አጠናቅቋል።

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን የተሳተፈው አትሌት ምስጋናው ዋቁማ በተርኪዬ አንታሊያ ከተማ ሚያዚያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው 30ኛው የዓለም አትሌቲክስ የእርምጃ ውድድር የቡድን ሻምፒዮና ላይ 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ51 ሴኮንድ በመግባት በርቀቱ የግሉን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቧል።

አትሌቱ የገባበት ጊዜ የኢትዮጵያ የርቀቱ ክብረ ወሰንም ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.