በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በነቀምቴ የተገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ የተገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ተመርቋል፡፡
በምርቃ ሥነስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የፌዴራልና ክልሎች ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
ፋብሪካው በቀን 420 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፥ ከ300 ሺህ ዳቦ በላይ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል ።
ፋብሪካው በከተማዋ ለሚገኙ 300 ወጣቶች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የስራ እድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።
በሌሊሴ ተስፋዬ