Fana: At a Speed of Life!

የኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡

በቤተ-ክርስቲያኗ የስብክተ ወንጌልና ሀዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ድጋፉን ባስከቡበት ወቅት÷ በጉዳቱ ቤተክርስቲያኗ ማዘኗን ገልጸው ለተጎጂ ወገኖች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

በቀጣይም ምዕመናኑን በማስተባበር ድጋፍ እንደሚደረግ መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የጎፋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ÷ ቤተ-ክርስቲያኗ አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ ተጎጂዎችን በማፅናናት ላደረገችው ያልተቋረጠ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉዳቱ የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽ ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ድጋፉም የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.