Fana: At a Speed of Life!

ጋርዲያን ሽልድ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ከገበያ ታገደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደረጃ በታች የሆነ እና ምንጩ ያልታወቀ ጋርዲያን ሽልድ የተሰኘ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ምርት በገበያ ላይ እንዳይውል መታገዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ አካሄድኩት ባለው የገበያ ኢንስፔክሽን ጋርዲያን ሽልድ ባለ 6 ቀዳዳ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ከጥራት ደረጃ በታች መሆኑ ስለተረጋገጠና ምንጩ ያልታወቀ ሆኖ በመገኘቱ ገበያ ላይ እንዳይውል ታግዷል፡፡

በዚህም ሚኒስቴሩ ይህንን ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል።

ማንኛውም ነጋዴም ሲሸጥ ቢገኝ ከፍትህ ተቋማት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አሳውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.