ደቡብ ኮሪያ በጎፋ ዞን ለደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ እንዳለው ድጋፉ የአደጋው የተጎዱ የአካባቢው ነዋሪዎችን ወደቀደመው ህይዎታቸው እንዲመለሱና አካባቢውን ወደነበረበት ለመመለስ ይረዳል ብሎ የሀገሪቱ መንግስት ተስፋ እንደሚያደርግም ነው የገለጸው፡፡
ዘ ኮሪያን ሔራልድ በጎፋ ዞን በአደጋው የሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውሶ ዘግቧል፡፡