በሕንድ በመሬት መንሸራተት አደጋ የ24 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ ደቡባዊ ግዛት ኬራላ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ24 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ66 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡
እየተከናወነ ያለውን የነፍስ አድን ሥራም የድልድይ መደርመስ እያስተጓጎለው መሆኑን ተከትሎ አደጋው በተከሰተበት ሥፍራ ያሉ ዜጎችን ለማውጣት ጊዜያዊ ድልድይ እንዲሠራ ጥያቄ መቅረቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የሕንድ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው÷ ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ተጎጅዎች ከ200 ሺህ እስከ 50 ሺህ ሩፒ ካሳ ይከፈላል ብለዋል፡፡