አሜሪካ በመንግስት ለተደረገው ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊነት ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የበለጠ ነፃ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በኢትዮጵያ መንግስት የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲሆን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር እንደምትደግፍ አረጋገጠች፡፡
ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ አካሄድ ከባድ ቢሆንም የተዛባውን የሀገሪቱን ማክሮ ኢኮኖሚ ለመጠገን ወሳኝ እርምጃ መሆኑን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መልዕክት ገልጿል፡፡
አሜሪካ የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲሆንም ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን ድጋፍ እንደምታደርግ ኤምባሲው ባወጣው መልዕክት አረጋግጧል፡፡