የጋምቤላ ክልል በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል።
የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር ዑሞድ ኡጁሉ፥ በደረሰው አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በጊዜያዊነት ከሚደረገው የ3 ሚሊየን ድጋፍ በተጨማሪ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለጹት፡፡
በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች መጽናናትን መመኘታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡