ኮሚሽኑ ከልማት አጋር አካላት ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (ዩኤን.ዲ.ፒ) በኩል ድጋፍ ከሚያደርጉ የውጭ የልማት አጋር አካላት ጋርተወያይቷል፡፡
ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ኮሚሽኑ ከድርጅቱ ጋር ካደረገው አራተኛው ዙር ውይይት በኋላ ያከናወናቸውን አበይት ተግባራት በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ገለፃውን የተከታተሉት የልማት አጋሮቹ የቀረበውን ማብራሪያ መነሻ አድርገው ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡
በኮሚሽኑና በምክክሩ ዙሪያ ከተሳታፊ አጋር ድርጅቶች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡