በአውስትራሊያ 500 ሺህ ዶላር የሚገመቱ ብርቅዬ የአዕዋፋት እንቁላሎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ 500 ሺህ ዶላር የዋጋ ግምት ያላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ብርቅዬ የአዕዋፋት እንቁላሎች መያዛቸው ተሰማ፡፡
በአውስትራሊያ በህገ ወጥ የአዕዋፋት ንግድ ላይ በተደረገ ዘመቻ ነው የተለያዩ የአዕዋፋት ዝርያዎች 3 ሺህ 404 እንቁላሎች ተከማችተው የተያዙት፡፡
እንቁላሎቹ ከ400 ሺህ እስከ 500 ሺህ ዋጋ እንደሚያወጡ የተነገረ ሲሆን፥ የተሰበሩና የተበላሹ ቢሆንም ለጌጣጌጥነት እንደሚውሉም ተገልጿል።
በዚህም የ62 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ግለሰብ በህገወጥ ንግድ ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ በዚህ ህገወጥ ድርጊት መሳተፍ እየተለመደ መምጣቱን ያነሳው ዘገባው፥ ለአካባቢና የዱር እንስሳት ለአደጋ መጋለጥ እንደምንያት የሚጠቀስ ነው ብሏል፡፡