ሉካ ሞድሪች ለተጨማሪ አንድ ዓመት ውሉን አራዘመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪያል ማድሪዱ አማካይ ሉካ ሞድሪች በሳንትያጎ ቤርናቢዩ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡
በፈረንጆቹ 2012 ከእንግሊዙ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው የ38 ዓመቱ ክሮሺያዊው አማካይ ሉካ ሞድሪች፤ ለ12 የውድድር ዓመታት የሎስ ብላንኮዎቹ የቡድን ድምቀት መሆን ችሏል፡፡
በቆይታው ከስፔኑ ሀያል ክለብ ጋር 6 የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ፣ 5 የክለቦች የዓለም ዋንጫ፣ 4 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫ፣ 4 የላ ሊጋ፣ 2 የስፔን የንጉስ ዋንጫ እና 5 የስፔን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል፡፡
ከክለብ በተጨማሪም በግሉ የ2018 የወርቅ ኳስ (ባሎን ድ ኦር)፣ በፊፋ የወንዶች የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች እና የአውሮፓ ዋንጫ ምርጥ ተጫዋች የሚል ሽልማትን ማሸነፍ መቻሉ ይታወሳል፡፡
ሞድሪች በሪያል ማድሪድ ቤት 534 ጊዜ ተሰልፎ 39 ጎሎችን ሲያስቆጥር ለሀገሩ 178 ጊዜ በመሰለፍ በብሔራዊ ቡድኑ ታሪክ ብዙ ጊዜ የተሰለፈ ተጫዋች ነው፡፡