በእድል ወይም በፈጣሪ ፍቃድ ተርፌያለሁ – ዶናልድ ትራምፕ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግድያ ሙከራ የተቃጣባቸው የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በእድል ወይም በፈጣሪ ፍቃድ ልተርፍ ችያለሁ ሲሉ ገለጹ፡፡
ትራምፕ በመጪው ህዳር ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ ነበር የግድያ ሙከራው የተደረገባቸው፡፡
ከግድያ ሙከራው በኋላም ጆሯቸው በጥይት ተጨርፎ ደም ሲታይ የነበረ ቢሆንም አይበገሬነታቸውን እጃቸውን ከፍ አድርገው ለታዳሚዎቻቸው እንዳሳዩ ማየት ተችሏል፡፡
የ78 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከክስተቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ቃለ ምልልስም ህይዎታቸው በዕድል ወይም በአምላክ ፍቃድ ሊትርፍ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በጥቃቱ ጥይቱ በቀላሉ ሊገድላቸው ይችል እንደነበር ገልጸው፥ ይህም ለእኔ እንደ ህልም ነው ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
በጥቃቱ አንድ ሰው ሲሞት ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፥ የ20 ዓመቱ ጥቃት አድራሹ ወጣት ቶማስ ማቲው ህይዎቱ እንዳለፈ ይታወቃል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስለደህንነታቸው ደውለው ስለጠየቋቸውም ምስጋና ማቅረባቸውን የዘገበው ዘ ቴሌግራፍ ነው፡፡