Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሸዋ ዞን የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም በምሥራቅ ሸዋ ዞን እና በአዳማ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ስራ አጥነትን ለመቀነስ በመገንባት ላይ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ተመልክተዋል፡፡

በአዳማ ከተማ አስተዳደር ከተጎበኙ ፕሮጀክቶች መካከል የዶሮና የወተት ላሞች እርባታ፣ ለስጋ እንስሳት ማድለቢያና ለአሳማ እርባታ የተገነቡ ማዕከላት እንደሚገኙበት ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ ለጎብኝዎቹ ባደረጉት ገለጻም በከተማው ለዶሮ፣ ለወተት ላሞች እርባታ፣ ለስጋ እንስሳት ማድለቢያና ለአሳማ እርባታ 1 ሺህ 445 ማዕከላት በመንግሥትና በባለሀብቶች ተሳትፎ ተገንብተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.