Fana: At a Speed of Life!

በትራምፕ የፌስቡክና ኢንስታግራም ገጽ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እና የአሁኑ እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕ የፌስቡክና ኢንስታግራም ገጽ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱ ተነገረ።

ሜታ ኩባንያ በትራምፕ የፌስቡክ እና የኢንስታግራም ገጾች ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ ያነሳው ትራምፕ በመጪው ህዳር ወር የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ለመመረጥ እየተፎካከሩ በመሆናቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገደብ የተጣለባቸው በፈረንጆቹ 2021 ጥር ወር ላይ የዋይት ሀውስ ቤተ-መንግስትን ደጋፊዎቻቸው በኃይል ሲወሩ ድርጊቱን አድንቀዋል በሚል ነው።

ሜታ ኩባንያ የገደቡን መነሳት አስመልክቶ፤ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮች ህብረተሰቡ እንዲሰማ እና አሜሪካውያን ከፕሬዚዳንታዊ እጩዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ያለምንም አድሎ መስማት አለባቸው ብሏል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

ኩባንያው በዚህ ምክንያት ገደቡን ቢያነሳም ፖሊሲውን የሚጻረሩ የጥላቻ ንግግር እና ሌሎች ጠብ አጫሪ መልዕክቶችን እንደማይታገስ አስታውቋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.