Fana: At a Speed of Life!

የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ዲፕሎማቱ በሀገር ፍቅር ስሜት ሊተጋ ይገባል – አምባሳደር ታዬ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ዲፕሎማቱ በሀገር ፍቅር ስሜት ሊተጋ ይገባል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናገሩ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች እና ቆንጽላዎች ለሚወክሉ አዲስ ለተሾሙ አምባሳደሮች ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

በስልጠናው መክፈቻ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት አምባሳደር ታዬ ÷የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቁ ሒደት ውስጥ ዲፕሎማቱ የሀገር ፍቅር ስሜትን ማስቀደም አለበት ብለዋል።

ኢትዮጵያ በታሪኳ ጠንካራ ዲፕሎማት እንዳላት በተለያዩ መስኮች አሳይታለች ያሉት ሚኒስትሩ÷ ይህንን ለማስቀጠልም ራስን በዕውቀት ማነጽ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የመሪነት ጥበብ ፣ታላቀት እና የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ መረዳት ከዲፕሎማቶቹ እንደሚጠበቅ አንስተዋል።

በዚህ አግባብ የሚጓዙ ዲፕሎማቶች ለሀገራቸው ዘብና ኩራት ናቸው ያሉት አምባሳደር ታዬ ÷ሀገርም ከአምባሳደሮቹ ብዙ ትጠብቃለች ብለዋል።

ስልጠናው ከሐምሌ 4 እስከ 20 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

በወንድሙ አዱኛ እና አልማዝ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.