Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የአፍሪካ ህብረት አመራሮችና የልማት አጋሮች በተኙበት ዛሬ ተካሂዷል፡፡

የመጀመሪያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከነሐሴ 29/2016 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ፎረሙ የበለጸገች እና እርስ በእርስ የተሳሰረች አፍሪካን እውን ለማድረግ የተቀረጸውን የአጀንዳ 2063 ዓላማን ከማስፈጸም አንጻር አስተዋጽዖው የጎላ መሆኑን የስራና ከተማ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሰኒ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያም ይህን አህጉራዊ መድረክ ከማስተናገድ ባሻገር ያላትን ምርጥ የከተማ ልማት ተሞክሮዎችን ለአፍሪካ ከተሞች የምታቀርብበት መድረክ ይሆናልም ነው ያሉት።

የፎረሙ ውጤትም አፍሪካውያን በአንድ አቋም የክትመት ምጣኔን የሚያጤኑበት እንዲሁም በአፍሪካ የክትመት ምጣኔና የከተማ ልማት መዋቅራዊ መፍትሄዎች ላይ የጋራ አቋም የሚያንጸባርቁ ውሳኔዎች የሚጸድቁበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.