Fana: At a Speed of Life!

 ሂዝቦላህ በእስራኤል የጦር ካምፖች ላይ ጥቃት መፈፀሙን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው የሂዝቦላህ ቡድን በእስራኤል የጦር ካምፖች ላይ መጠነ ሰፊ የአፀፋ ጥቃት መፈፀሙን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አደረገ፡፡

ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ በሰሜናዊ እስራኤል በሚገኙ ሶስት የጦር ሰፈሮች ላይ የአፀፋ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።

ቡድኑ እንዳስታወቀው፤ ከአንድ ቀን በፊት በእስራኤል አይሌት፣ ሜሮን እና ኒምራ የተባሉ የጦር ሰፈሮች ላይ ከመቶ በላይ ሮኬቶችን በማስወንጨፍ የተሳካ ዘመቻ አካሂዷል።

ሂዝቦላህ ባደረገው የአጸፋ ጥቃት አንድ አሜሪካዊን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል በሚፈፅመው ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት ከ2 ሺህ 500 በላይ እስራኤላውያን አካባቢውን ለቀው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡

የሂዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥ የነበረው ሞሃመድ ኒማህ ናስር በእስራኤል መገደሉን ተከትሎ ቡድኑ ባለፉት አምስት ቀናት ተከታታይ የአፀፋ ጥቃት በእስራኤል የጦር ሰፈሮች ሲፈፅም ቆይቷል፡፡

የቡድኑን ጥቃት ለመከላከል እስራኤል የምትሰጠው ምላሽ ሊባኖስን ለከፍተኛ ውድመት ሊዳርጋት እንደሚችል ስጋት መፈጠሩን የሊባኖሱን አል ማይዲ የዜና ምንጭን ጠቅሶ ፕሬስ ቴቪ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.