Fana: At a Speed of Life!

አሥተዳደሩ በሕጻናት ላይ አተኩሮ እያከናወነ ላለው ሥራ ስኬት ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በልዩ ሁኔታ ለሕጻናት ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነው ያለው ተግባር ከስኬት እንዲደርስ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ፡፡

በደብረ ብርሃን እና አሰላ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት በአማርኛ እና ኦሮምኛ ቋንቋዎች ሥርዓተ-ትምህርት በዲፕሎማ መርሐ-ግብር ስልጠና ተከታትለው ያጠናቀቁ 2 ሺህ 27 የቅድመ 1ኛ ደረጃ መምህራን በዓድዋ ድል መታሰቢያ መመረቃቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

የመርሐ-ግብሩ ዋና ዓላማም አዲስ አበባ ሕጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ የጀመርነውን ራዕይ ማሳካት ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ዛሬ ያስመረቅናቸውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ዙሮች 3 ሺህ 685 መምህራንን አስመርቀን ወደ ሥራ አስገብተናል ነው ያሉት፡፡

ከተማ አሥተዳደሩ ሕጻናት ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ እያከናወነው ያለው ሥራ ስኬታማ እንዲሆን ያልዘራነውን እንደማናጭድ በመገንዘብ ሁላችንም ድጋፍ እናድርግ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.