ቢሮው በተለያዩ ተቋማት ያስተማራቸውን መምህራን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ በደብረ ብርሃን እና አሰላ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ያስተማራቸውን 2 ሺህ 27 የቅድመ 1ኛ ደረጃ መምህራን እያስመረቀ ነው፡፡
የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ እየተካሄደ የሚገኘው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝዬም አዳራሽ መሆኑን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡