Fana: At a Speed of Life!

ማሱድ ፔዜሽኪያን የኢራን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የለውጥ አቀንቃኙ ዶክተር ማሱድ ፔዜሽኪያን ተፎካካሪያቸውን ወግ አጥባቂውን ሳኢድ ጃሊሊን በማሸነፍ የኢራን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

በምርጫው በተሰጠው ድምጽ ዶክተር ፔዜሽኪያን 53 ነጥብ 3 በመቶ ሲያገኙ፤ ተፎካካሪያቸው ጃሊሊ 44 ነጥብ 3 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የምርጫው ውጤት ይፋ ከመሆኑ አስቀድሞ የዶክተር ፔዜሽኪያን ደጋፊዎች በቴህራንና ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች አደባባይ በመውጣት ደስታቸውን ሲገልጹ እንደነበር ተገልጿል።

የ71 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋና የልብ ቀዶ ህክምና ባለሙያው ተመራጩ ፕሬዚዳንት፤ የኢራን ፓርላማ አባል ናቸው።

ይህ ምርጫ የተካሄደው በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸውን ያጡትን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲን ለመተካት መሆኑ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.