Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በቀን፣ በማታ፣ በቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በክረምት መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 688 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 269 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

እንዲሁም ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 596 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን÷ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲም በመደበኛና በተከታተይ መርሐ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.