Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ ፡፡

በዛሬው ዕለት የአርባ ምንጭ፣ የሀዋሳ፣ የወላይታ ሶዶ፣ የዲላ፣ የጂንካ፣ የአዲግራት፣ወራቤ፣ ወሎ፣ ደብረ ብርሃን፣ ወልድያ እና እንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን የቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል፡፡

በዚህም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር በተለያዩ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 859 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲም በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ከ4ሺህ 800 በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛ ቅድመ ምረቃ መርሐ ግብር ያሰለጠኗቸውን 2ሺህ 356 ተማሪዎችን ማስመረቁን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

እንዲሁም ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና ድህረ ምራቃ ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ 589 በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስተምራቸው የቆዩ 1ሺህ 114ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

በተጨማሪም በአማራ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ወሎ፣ደብረ ብርሃን፣ወልድያ እና እንጅባራ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮችያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል፡፡

እንዲሁም አምቦ እና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች ማስመረቃቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡

ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ የሙያ መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 2ሺህ 115 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በጎህ ንጉሱ ፣ማቲዎስ ፈለቀ፣ ኢብራሂም ባዲና ኤርሚያስ ቦጋለ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.