ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ወ/ሮ ሽዊት ሻንካ – የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር
2. ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) – የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር
3. አቶ ቀጀላ መርዳሳ – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡
ሹመቶቹ ከሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የተሰጡ መሆኑንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡