ሐረር የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያንን ተቀበለች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ26ኛው ዓለም አቀፍ የሀረር ቀን ለመሳተፍ ከተለያዩ ዓለማት ወደ ሀገር ቤት የገቡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ሐረር ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ያደረጉት ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል እንዲሁም በ26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደ ሀገር ቤት የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዲያስፖራዎች ሐረር ከተማ ሲደርሱ በክልሉ መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል ነው የተባለው።
26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር እንደሚጀምር ከከተማው አስተዳደር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።